Read their Story! We would love to share how God has been using VBC to impact the students’ life for His Kingdom. We are excited to share how their lives are making a difference in the church, their community, and the world.

Hiwot Gebeyehu Utalo
from Winnipeg, Manitoba, Canada.
Registered Nurse
I am so grateful to the teachers and staff at the College for giving me the incredible opportunity to grow in my Christian faith and deep root my knowledge in theological understanding.
My name is Hiwot Gebeyehu Utalo, and I am a wife, mother of three kids, and a Registered Nurse living in Winnipeg, Manitoba, Canada. I have recently graduated from Vision Bible College and currently studying MEd SCI at Cape Breton University. My experience at the Vision Bible College was so uplifting. I am so grateful to the teachers and staff at the College for giving me the incredible opportunity to grow in my Christian faith and deep root my knowledge in theological understanding. They influenced me in several aspects, not only in teaching biblical lessons but also by showing Godly characters, personalities, attitudes and moral conduct! I can never thank them enough for every good thing they invested in me, so I continue to reflect Jesus’ image in my life! Learning the foundation of my faith, including forgiveness, forbearance, love, and respect, is something that encouraged me to continue pursuing God and seeking his purpose in my life! Indeed, attending the Vision Bible College gave me the opportunity of a lifetime.

Lucia Mishima
British Columbia, Canada
works on the Banking Industry
VBC also have a great administration and well organized Live Stream Teaching Style so that anyone can learn from anywhere
ስሜ ሉቺያ ምሥጉን ይባላል ። ባለትዳርና የልጆች እናት ነኝ ። ኗሪነቴ በ British Colombia ግዛት Canada Fort St. John በምትባል ከተማ ነው።በትምህርቱ ዓለም ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በ Computer Science በCanada ከምትገኘው ከ Northern Light Collage በ Business Management በ Accounting major የተመረኩ ሲሆን በዚሁ ሙያ ተሠማርቼም ሠርቻለሁ።
በአገልግሎቱም ዘርፍ ባለቤቴ በምንኖርበት ከተማ በ Peace Lutheran Church በመጋቢት ሲያገለግል እኔም በአምልኮ መሪነት ፥ በድቁና ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በመሪነትና በመሳሰሉት የአገልግሎት ዘርፎች አገለግላለሁ በማህበረ ሰብ አገልግሎት ደግሞ በ Community Breakfast Ministry በመሪነት አገለግላለሁ ። በሀገር ደረጃ በሚካሄድ በማላጅ የፀሎት ፕሮግራም እሳተፋለሁ ።
መቼም በ Vision Bible College የሁለት ዓመት ኮርስ ብዙ ነገሮችን ቀሰሚያለሁ ፤ ብዙ ነገርም በውስጤ ቀርቷል ። የት/ቤቱ ዋና ዓላማ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያውቁና በቃሉ እንዲያድጉ ስለሆነ በእርግጥ ይሄ ት/ቤት ተሳክቶለታል ብዬ እላለሁ ።
በአንደኝነት ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስ የሥርዓት መጽሐፍ በመሆኑ ኋሳቡንም ለመረዳት በአጠቃላይ ምዕራፉን ማንበብና ሙሉ ሀሳቡንም ለማግኘት አጠቃላይ ፖዝሉን ገጣጥመን ማንበብ እንዳለብን እንጂ ቁንጽል ሀሳብ ይዘን እንዳንመላለስ ለማወቅ ረድቶኛል ። ይሄም ደግሞ Name it claim it ከሚለው ከማይጨበጥ ነገር እንደሚታደገን ተረድቻለሁ ።
በሁለተኛ ደረጃ በሁሉም አቅጣጫ የአመለካከት ዕይታዬን ቀርጾታል። ይልቁንም እኔ ከማውቀውና ከምረዳው በላይ የእግዚአብሔር ፀጋ በሰዎች ላይ ሊገለጽና ሊሠራ አንደሚችል በመረዳት ከመተቸትና ከመፍረድ እንድቆጠብ እረድቶኛል ።
3ኛ በዚህ ተ/ቤት ሁለገብ የሆነ ትምህርት ስለሚሰጥ ከዚህ የተነሳ የሥነ ምግባር አስፈላጊነት በሕብረተሰብ ና በቤተሰብ መካከል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ቤተሰብና ልጆች እንዴት እንደሚመሩ ፤ አኔ እንደ አንድ ግለሰብ በሀገርና በመንግሥት አካል ውስጥ ገብቼ እንዴት ተጽዕኖ ማምጣት እንደምችል ተረድቻለሁ ። ከዚህ ቀደም በዚህ ዙሪያ የነበረኝን እምነትና ዕይታ በብዙ መልኩ ለውጦታል ።
በመዝሙረ ዳዊት 119:32 ላይ ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ በትእዛዝህ መንገድ ሮጥሁ እንደሚለው ቃል ማስተዋል ተጨምሮልኝ አይቻለሁ ። በተጨማሪም በተለይ የወንጌል ስርጭት ኮርስ ላይ እንዴት መመስከር እንዳለብን በተማርኩት መሠረት ያንን ዘዴ በመጠቀም ለሁለት ሰዎች መስክሬ ወደ ጌታ እንዲመጡ የክትትልትምህርት እንዳስተምራቸውና እንዳሳድጋቸው እረድቶኛል ።በአጠቃላይ ስለ መምህራኑ ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል ። ትህትናቸው ና ትዕግሥታቸው ከአንዲት እናት ማህፀን የወጡና በአንድ ላይ ያደጉ እስኪመስል ድረስ ይመሳሰላሉ ። የተለያየ ዶክትሪን ያለንን ሰዎች እምነት ሳይነኩ በፍቅርና በትህትና እንደየሁኔታችን ጠቦቱን እንደጠቦትነቱ ፥ ግልገሉን እንደግልገልነቱ ፥ እንዲሁም በጉን እንደበግነቱ በቀስታ እየመሩ እግዚአብሔር ወደሚፈልገው የህይወት ጎዳና መርተውናል / አሳድገውናል ።
ጊዜን መስጠት ከባድ በሆነበት በዚህ የሰሜን አሜሪካ ኑሮ ጊዜያቸውንና ማንነታቸውን ሰጥተው በትጋት እንዳስተማሩን የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ እንደሠሩ ታማኙ አምላክ ደግሞ የእነሱን ቤት እንደሚሠራላቸው አምናለሁ መልካምን ነገር ዘርተዋልና መልካምን ነገር ያጭዳሉ ። በነፃ የተቀበሉትን በነፃ እንደሰጡ እኔም የነሱን ፈለግ እንድከተል ፈጣሪ ይርዳኝ።
በዚህ Bible College የተዋወቅኳቸው ቅዱሳን በጣም በፍቅር የተሞሉ ፤ በዙ የታመቀ የእግዚአብሔር ፀጋ ያላቸው ናቸው። ለወደፊትም አብረን በፀሎት ህብረት ለመቀጠል ወስነናል ። በዚህ የኮሌጁ Alumni ላይ ጌታ በሰጠን ፀጋ በመሳተፍ እናገለግላለን
የዚህ ራዕይ መሥራቾችን እግዚአብሔር አምላክ ይባርክ ።

መጋቢ መንግሥቱ ሃብታሙ
አውስትራሊያ ሜልበርን
ከእውቀት አለም የቀዱ ከመንፈስ አለም የተነካኩ ለመሆናቸው እንደኔ ተጠግቶ ወይም እግራቸው ስር ቁጭ ብሎ የተማረ ሰዉ ብቻ ነው እምለውን ሊረዳ የሚችለው
በቪዥን ባይብል ኮሌጅ በመማሬ የተጠቀምኩትን ለመፃፍ በተለይ የእያንዳንዱ አስተማሪ በኔ ላይ ያመጣዉን በጎ ተፅእኖዎች መፅሀፍ ከልፃፍኩኝ በስተቀር በቀላል እሚቋጭ አይደለም።
በአጭሩ ለመናገር ከእውቀት አለም የቀዱ ከመንፈስ አለም የተነካኩ ለመሆናቸው እንደኔ ተጠግቶ ወይም እግራቸው ስር ቁጭ ብሎ የተማረ ሰዉ ብቻ ነው እምለውን ሊረዳ የሚችለው። በተላይ ሁል ጊዜ የሚገርመኝ በጣም የተማሩ እና በጌታ ቤት በማገልገል ብዙ ልምምድ ያላቸው ሆነዉ እንደኔ ያለ ትንሽ የመላምት ሀሳብ ለማንሸራሸር ያላቸው የልብ ስፋት እና ትህትና ልረሳዉ አልችልም።
ይህንን ስል ከልቤ መሆኑን እምታዉቁበትን ቀላል ማስረጃ ላቅርብ። ትምህርት የሚሰጠዉ ከካናዳ ነዉ እኔያለሁት አውስትራሊያ ነው ሰዓታችን ፈፅሞ አይገናኝም ነገር ግን ከለቀቁብኝ መንፈሳዊ ረሃብ የተነሳ ትምህርቴ የጨረስኩት በአዉስትራሊያ ሰአት አቆጣጠር ለሊት ለሊት በአብዛኛዉ 2am-4am ነበር። ያ ማለት ሊነጋ ሲል ነዉ የምተኛዉ።
ሌላው ሳልገልጽ የማላፈዉ በቪዥን ባይብል ኮሌጅ ተማሪዋች የሚከፍሉት በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ እኔ ደግሞ መማር የጀመርኩበት ጊዜ ወቅቱ በኮቪድ የኢኮኖሚ ጫና ስለነበረ ለኔ ግማሽ ክፍያ ተደርጎልኝ ነዉ የጨረስኩ ለዚም ጌታ ይባርካቹ ማለት እፈልጋለሁ።
በመጨረሻ ይህንን መልእክቴን የምታነቡ ቅዱሳን በሙሉ እናም እንደኔ ጌታን ለማገልገል እጣ የወደቀባቹ እዚህ ኮሌጅ ገብታችሁ እንድትማሩ በሀይል አበረታታለሁ።
” በኮሌጅ ዉስጥ ሳይሆን ያለፍኩት ኮሌጁ በኔ ዉስጥ አልፎአል “

Thomas Belayneh
from Calgary, Canada.
Thechnology Support Specialist
ህያው የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል መማር ትልቅ መታደል ሲሆን ማንኛውም አማኝ ከጥፋት ወይም ከስህተት ትምሀርት ራሱንም ቅዱሳንን ለመታደግ እንዲማር በጌታ ፍቅር እመክራለሁ።
ብዙ ጊዜ የመፅሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር ትልቅ መሻት ቢኖረኝም የጌታ ፍቃድ በቪዥይን ባይብል ኮሌጅ እንድማር በመሆኑ ጌታን እጅግ አመሰግናለሁ።“ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና። ፊልጵስዩስ 2፡13”
በዚህ አጋጣሚ ብዙ ትምህርትቶችን ተምሬአልሁ የወንጌል ስርጭት ተግባራዊ የሆኑ እርምጃዎች የሆኑትን ለምሳሌ ክርስቶስን የማያውቁ ሰዎች የምትችለውን ያህል ስም ዘርዝረህ ፃፍ፣ በየዕለቱ ፀልይላቸው፣ለነዚህ ሰዎች ለመመስከር ቀንና ሰዓት ወስን የሚል ጠቃሚና ተግባራዊ እርማጃዎችን በህይወቴ ወንጌል ለሰዎች ለማድረስ ዕውቀትን ጨምሮልኛል።
በተለይም ህያው የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል መማር ትልቅ መታደል ሲሆን ማንኛውም አማኝ ከጥፋት ወይም ከስህተት ትምሀርት ራሱንም ቅዱሳንን ለመታደግ እንዲማር በጌታ ፍቅር እመክራለሁ።በዚህ አጋጣሚ ይህንን ትምህርት ከባለቤቴ ጋር አብረን ስለተማርን ለትዳራችንም ለልጆቻችን የትምህርት አስፈላጊነት እንድናውቅ እረድቶናል። በመጨረሻውም አስተማሪዎቻችንና እጅግ እናምሰግናቸዋለን።

Reshan Mesfin
from Calgary, Canada.
Assistance Nurse
በጣም ተጠቅሜበታለው፣ ተምሬበታለው፣ ተለውጬበታለው፣ ሕይዎቴ ተቀይሯል፣ አድጌበታለው እና እናንተም እንድተማሩ አበረታታለው፡፡ እንዳያመልጣችሁ ተመዘገቡ፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ሰላምታ አቀርባለው
ሥሜ ተማሪ ርሻን መስፍን ይባላል፡፡ የ ቪዥን ባይብል ኮሌጅ ተማሪ ነኝ፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት ለሁለት ዓመት ስማር ብዙ የሕይወት ለውጥ የአይኔ መከፈት አይቼበታለው፡፡ ሕይዎቴ ከጌታ ጋር እንዴት መጣበቅ እንዳለብኝ ቤተሰቤ መምራጥ፣ ልጆቼ በእግዚአብሄር ቃል ለማሳድግ እንዴት እንደምችል በሙሉ ተምሬበታለው፡፡ ጌታን እስከአሁን ድርስ አውቀው ነበር ወይ? እስክምል ደርስ ያስተማሩኝ አስተማሪዎች ሕይወታቸውን ቆርሰው፣ ሕይወታቸውን ራሱ ምስክርነት የሆነ አርአያዎች የሆኑ እንደ እነ ፓስተር ተርፈ፣ ፓስተር አስራት ሌሎችም ብዙዎች ናቸው በጣም ተጠቅሜበታለው፣ ተምሬበታለው፣ ተለውጬበታለው፣ ሕይዎቴ ተቀይሯል፣ አድጌበታለው እና እናንተም እንድተማሩ አበረታታለው፡፡ እንዳያመልጣችሁ ተመዘገቡ፡፡
አስተማሪዎቼ ጌታ ይባርካቸሁ በጣም አምስናለው፡፡ ተባርኩ፡፡

Solomon Tesfay
from Colombus, USA.
Church Leader
ጌታን እንዴት ሆኜ ማገልገልና ክርስትናን እንዴት ሆኜ እንደምኖር አስተምረውኛል:: ሌሎችም እንድሁ እንደኔ እንዲጠቀሙ እመክራለሁ::
ስሜ ሰሎሞን ተስፋይ ይባላል::
የምነረው በኣሜሪካ ኮሎምቦስ ከተማ ነው:: የማገለግለው በፊላደልፍያ ወንጌላዊት በቴክርስትያን ሲሆን አገልግሎቴ ቃል በማስተማር እና የቤተክርስቲያኒቱ ሽማግሌ በመሆን ነው:: በቪዥን በግሌ የተጠቀምኩት ነገር ካለ አስተሳሰቤ ሙሉ ለሙሉ መቀየሩ ነው።በጌታ ቤት 27 ዓመት ሆነኛል። ጌታን ሳገለግለው ብዙ የማውቅ ይመስለኝ ነበር።አሁን ግን ሆኜ ሳስብና ሳየዉ ግን ጌታ እና ትምህርቱ የማይደረስ መሆኑን ነው የተማርኩት።እና በዚህ የነበረኝ ኣስተሳሰብ እንዲቀየር ኮሌጁ ረድቶኛል።
ከኣስተማሪዎቼ የተማርኩት ከሁላቸውም ያየሁት ነገር በትምህርቱ የበሰሉና ብቃት ያላቸው መሆኑን ነው:: ከትምህርቱ ይልቅ ግን በፍቅርን እና ትህትና የተመረቁ መሆናቸው ደግሞ አይቻለሁ:: ጌታን እንዴት ሆኜ ማገልገልና ክርስትናን እንዴት ሆኜ እንደምኖር አስተምረውኛል:: ሌሎችም እንድሁ እንደኔ እንዲጠቀሙ እመክራለሁ::

ኤልሳ ዘርጋው
ነርስ፤ ከኤድመተን ካናዳ
በትምህርቱም የእግዚአብሔርን ቃል በስፋት እንዳውቅና እንዴት መኖር እንዳለብኝ ተምርያለሁ::
ኤልሳ ዘርጋው እባላለሁ:: የምኖረው በኤድመንተን ካናዳ ሲሆን በስራዬ ነርስ ስሆን የማመልከዉና የማገለግለው ደግሞ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ነው:: በዚህ ኮሎጅ በሰርተፍኬትም በዲፕሎማም ተምርያለሁ:: በትምህርቱም የእግዚአብሔርን ቃል በስፋት እንዳውቅና እንዴት መኖር እንዳለብኝ ተምርያለሁ:: ይህም ትምህርት ለመንፈሳዊ ህይወቴ ብቻ ሳይሆን በስራዬም ከሌሎች ጋር ላለኝ ግንኙነት ሁሉ ጠቅሞኛል:: አስተማርዎችም ያካፈሉን እውቀት ብቻ ሳይሆን የህይወት ልምዳቸውንና ፀጋቸውን በመሆኑ በጣም ተጠቅምያለሁ:: ይህንን እድል ሌሎች እንዲጠቀሙ በብርቱ አበረታታለሁ::

Adiam Atsbha
Assistance Nurse, Maryland USA
The teachers are not only Teachers of the word of God, but they are great Examples of the Living Christ.I have seen Christ in them. They thought us out of their Life Experience.
May the Peace and Grace of God be with all you. My name is Adiam Atsbha I live in Maryland USA. I am
a Diploma Graduated Student from Vision Bible College of Edmonton.
In this short statement, I want to share my journey in this amazing and eye-opening learning experience
in this college. VBC is a visionary College as its name indicates. It is making an impact in this generations.
It is a place where you get a great understanding of the word of God and God’s heart for us as Christian
of good Stewards of the great Commission.
The teachers are not only Teachers of the word of God, but they are great Examples of the Living Christ.
I have seen Christ in them. They thought us out of their Life Experience.
In addition to this VBC also have a great administration and well-organized Live Stream Teaching
program. Any one can learn literally from around the world in the comfort of their house.
As the Apostle John wrote on his book…..
“Jesus did many other things as well. If every one of them were written down, I suppose that even the
whole world would not room for the books that would be written.
John 21:25 without any exaggeration I felt like the apostle. I can’t share all of my experience the impact
in my life in this short statements. If you really are looking for a Bible College register, as soon as you can
before it will be full.
GOD BLESS YOU ALL
JESUS IS COMING SOON
MARANATHA!

Anteneh Kassahun
VIsual Merchandise Coordinater
United Arab Emirates
ዳዊትም፦ የሥራውን ሁሉ ምሳሌ አውቅ ዘንድ ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር እጅ ተጽፎ መጣልኝ አለ።”
1ኛ ዜና 28፥19
በአለም ላይ በተከሰተው covid19 ምክንያት በብዙ የአገልግሎት ዘርፍተጠቂ የነበረችው የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።
በዚህ ትልቅ ተግዳሮቶችን አሳልፋለች ከዚህም በዋነኝነት ደረጃ ህብረት ማድረግ አለመቻል ነበር ።
እኔም እነዚህ ችግሮች ሰከን ባሉበት 2021 አካባቢ ነበር V.B.C በማህበራዊ መገናኛ Facebook ላይ አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ማስተዋቂያ ሲነገር የሰማሁት በዚህም ብዙ ርቀት ካሉ ቅዱሳን ጋር ህብረት እንዳደርግ ረድቶኛል።
በነበረኝ የትምህርት ቆይታ በብዙ መልኩ ራሴን በእግዚአብሔር ቃል
መመልከት እንድችል የክርስቶስ አካል አገልጋይ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ለማገልገል ምን አይነት ዋጋ እንደሚጠይቅ እንዲሁም ቤተሰቤን ልጆችን እንዴት አድርጌ መያዝ እንዳለብኝ ረጅም ጊዜ አብሮኝ የኖረውን መፅሃፍ ቅዱስ እንዴት አድርጌ ማጥናት እንደምችል ተምሬበታለሁ ።
ከዛም ባሻገር ካለብኝ የስራ ጫና እንዲህም የትምህርት ሰአት ማዛባት በብዙ ተግዳሮት ትምህርቱን እንድጨርስ ላደረጉኝ ዋነኛ ምክንያቴ ውስጥ ለእያንዳንዱ የትምህርት ክፍልለ ጊዜ የሚመደቡልን አስተማሪዎች በነበራቸው የማስተማር ብቃት እና ቆይታ መልካም ወንድሞች ጓደኛ መካሪ እንዲሁም
ባለራዕይ መጋቢዎቹ እና ብዙ ፍቅር ያየንባቸው አስተማሪዎች ነበሩ ።
በእነርሱ በመማሬ እንደ አንድ ትልቅ ስኬት ህይወቴ እንደደረሰ እቆጥረዋለሁኝ። በዚህ በሰሜን አሜሪካ ያለች የሀገሬ ቤተክርስቲያን ብዙ መስራትና ማገልገል እንደ ምችል ብዙ ሰራተኞች ያሉባት መሆኗን ተረድቻለሁ ።
በመጨረሻም ለኤድመንት ቤተክርስትያን መሪዎች ልዩ ምስጋና አቀርባለሁ ።