Read their Story! We would love to share how God has been using VBC to impact the students' life for His Kingdom. We are excited to share how their lives are making a difference in the church, their community, and the world.

በቪጅን የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርትቤት መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም የተማርኩት:: እንደ አማኝ እንደ ሚስት እንደ አገልጋይ እንደ ቤተክርስትያን መሪ እንደ ባለራዕይ ሊኖረኝ የሚገባውን እውቀትና የህይወት ክህሎትም ጭምር እንጂ::
በቪዥን የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርትቤት በነበረኝ የሁለት አመት ቆይታየ የተካፈልኩትን የህይወትና የእውቀት መዓድ ላካፍላችሁ::
ስሜ ሰላም ግርማይ ይባላል:: ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት ነኝ:: ነዋሪነቴ ደግሞ በካልጋሪ ከተማ ነው::
በሞያየ በprenatal and postnatal department በነርሲንግ አገለግላለው::
በመንፈሳዊው አለም አገልግሎት ደግሞ በፊላደልፊያ ቤተክርስትያን በሚድያ ዲፓርትመንት ላይ በመሪነት በሽምግልና እና በመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት መሪነት ከእግዚአብሔር በሆነ ፀጋ አገለግላለው::
ስለራሴ ይህን ያክል ካልኩ ላካፍላቹ ወደ ወደድኩት ሃሳብ ልግባ::
በቪዥን ባይብል ኮሌጅ በነበረኝ የሁለት አመት ቆይታየ ከመምህራኑ ጅምሮ በእያንዳዱ ሂደት እጅግ በጣም ገንቢና እሚያንፅ ነበር::
ለሚጠየቁት ጥያቄዎችና አንዳድ የመወያያ ርዕሶች ጥበብና ማስተዋል የተምላው የመልስ አሰጣጥ የመምህራኑ ብቃትና ቅድመ ዝግጅት ያሳያል:: ከእውቀታቸውና ከህይወት ልምዳቸው በሚያስደንቅ ፍቅር: ትህትና እና ታጋሽነት አካፍለውናል::
በቪጅን የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርትቤት መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም የተማርኩት:: እንደ አማኝ እንደ ሚስት እንደ አገልጋይ እንደ ቤተክርስትያን መሪ እንደ ባለራዕይ ሊኖረኝ የሚገባውን እውቀትና የህይወት ክህሎትም ጭምር እንጂ:: መምህራኑ በህይወታቸው ከኖሩት ተፈትነውም ካለፉት በስህተታቸው ደግሞ ከተማሩት እና እነሱን ያገኘ እንቅፋት ሌላውን እንዳያገኝ ታሳቢ በማድረግ በብዙ ትህትና ርህራሄ ነበር ያስተማሩን:: ትምህርት ዲሲፕሊን ነው ይህ ማለት ደግሞ ጊዜ መስጠት ማለት ነው :: በዚህች አለም ደግሞ እምንፈተነው በጊዜ ነው:: እነዚህ ወገኖች ከእለት ሩጫቸው ከአገልግሎት ከቤተሰባቸው ጊዜ ቀንስሰው ትውልድንና ነገን በማሰብ መቆረስ መቻላቸው ክብሩ ለጌታ ጥቅሙ ደግሞ ለነዚህ ብሩካን ይሁንን እላለው::

I am so grateful to the pastors/teachers and registrars at the college for giving me this amazing opportunity to grow me in my spiritual walk with God. Instilling in me great knowledge in theological understanding enabled me to feel even more the presence of God in my life and made me trust Him completely.
My name is Mimi Gebregiorgis.i am graduating with a diploma program with vision Bible
college, the best move I have ever made for me. I am married and have three wonderful boys ages 18, 16, and 14. I live in Grande Prairie Alberta. I am the restaurant manager at Denny’s Family Restaurant. I enjoy spending time with my family and friends. Working in the restaurant, I work with and meet many wonderful people. It gives me the opportunity to pray for people and my employees, I try to let them see Jesus in everything I do.
The pastors/teachers at Vision Bible College are amazing scholars. I love how all the teachings were done in my own language giving me a better understanding of the teachings. They not only taught me about the Bible, they led me and guided me by using examples from their own lives giving me encouragement, enlightening me how in different trials and tribulations on how to still walk with God even when times are tough. I love and respect each one of the pastors/teachers and I am so grateful and honored to have them in my life today. I will never forget all that you have done for me.
Thank you!

I am so grateful to the teachers and staff at the College for giving me the incredible opportunity to grow in my Christian faith and deep root my knowledge in theological understanding.
My name is Hiwot Gebeyehu Utalo, and I am a wife, mother of three kids, and a Registered Nurse living in Winnipeg, Manitoba, Canada. I have recently graduated from Vision Bible College and currently studying MEd SCI at Cape Breton University. My experience at the Vision Bible College was so uplifting. I am so grateful to the teachers and staff at the College for giving me the incredible opportunity to grow in my Christian faith and deep root my knowledge in theological understanding. They influenced me in several aspects, not only in teaching biblical lessons but also by showing Godly characters, personalities, attitudes and moral conduct! I can never thank them enough for every good thing they invested in me, so I continue to reflect Jesus’ image in my life! Learning the foundation of my faith, including forgiveness, forbearance, love, and respect, is something that encouraged me to continue pursuing God and seeking his purpose in my life! Indeed, attending the Vision Bible College gave me the opportunity of a lifetime.

VBC also have a great administration and well organized Live Stream Teaching Style so that anyone can learn from anywhere
ስሜ ሉቺያ ምሥጉን ይባላል ። ባለትዳርና የልጆች እናት ነኝ ። ኗሪነቴ በ British Colombia ግዛት Canada Fort St. John በምትባል ከተማ ነው።በትምህርቱ ዓለም ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በ Computer Science በCanada ከምትገኘው ከ Northern Light Collage በ Business Management በ Accounting major የተመረኩ ሲሆን በዚሁ ሙያ ተሠማርቼም ሠርቻለሁ።
በአገልግሎቱም ዘርፍ ባለቤቴ በምንኖርበት ከተማ በ Peace Lutheran Church በመጋቢነት ሲያገለግል እኔም በአምልኮ መሪነት፣ በድቁና፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ በመሪነትና በመሳሰሉት የአገልግሎት ዘርፎች አገለግላለሁ በማህበረ ሰብ አገልግሎት ደግሞ በ Community Breakfast Ministry በመሪነት አገለግላለሁ ። በሀገር ደረጃ በሚካሄድ በማላጅ የፀሎት ፕሮግራም እሳተፋለሁ ።
መቼም በ Vision Bible College የሁለት ዓመት ኮርስ ብዙ ነገሮችን ቀስሚያለሁ ፤ ብዙ ነገርም በውስጤ ቀርቷል ። የት/ቤቱ ዋና ዓላማ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንዲያውቁና በቃሉ እንዲያድጉ ስለሆነ በእርግጥ ይሄ ት/ቤት ተሳክቶለታል ብዬ እላለሁ ።
በአንደኝነት ደረጃ መጽሐፍ ቅዱስ የሥርዓት መጽሐፍ በመሆኑ ኋሳቡንም ለመረዳት በአጠቃላይ ምዕራፉን ማንበብና ሙሉ ሀሳቡንም ለማግኘት አጠቃላይ ፖዝሉን ገጣጥመን ማንበብ እንዳለብን እንጂ ቁንጽል ሀሳብ ይዘን እንዳንመላለስ ለማወቅ ረድቶኛል ። ይሄም ደግሞ Name it claim it ከሚለው ከማይጨበጥ ነገር እንደሚታደገን ተረድቻለሁ ።
በሁለተኛ ደረጃ በሁሉም አቅጣጫ የአመለካከት ዕይታዬን ቀርጾታል። ይልቁንም እኔ ከማውቀውና ከምረዳው በላይ የእግዚአብሔር ፀጋ በሰዎች ላይ ሊገለጽና ሊሠራ አንደሚችል በመረዳት ከመተቸትና ከመፍረድ እንድቆጠብ እረድቶኛል ።
3ኛ በዚህ ት/ቤት ሁለገብ የሆነ ትምህርት ስለሚሰጥ ከዚህ የተነሳ የሥነ ምግባር አስፈላጊነት በሕብረተሰብና
በቤተሰብመካከል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ቤተሰብና ልጆች እንዴት እንደሚመሩ ፤ አኔ እንደ አንድ ግለሰብ በሀገርና በመንግሥት አካል ውስጥ ገብቼ እንዴት ተጽዕኖ ማምጣት እንደምችል ተረድቻለሁ ። ከዚህ ቀደም በዚህ ዙሪያ የነበረኝን እምነትና ዕይታ በብዙ መልኩ ለውጦታል ።
በመዝሙረ ዳዊት 119:32 ላይ ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ በትእዛዝህ መንገድ ሮጥሁ እንደሚለው ቃል ማስተዋል ተጨምሮልኝ አይቻለሁ ። በተጨማሪም በተለይ የወንጌል ስርጭት ኮርስ ላይ እንዴት መመስከር እንዳለብን በተማርኩት መሠረት ያንን ዘዴ በመጠቀም ለሁለት ሰዎች መስክሬ ወደ ጌታ እንዲመጡ የክትትል ትምህርት እንዳስተምራቸውና እንዳሳድጋቸው እረድቶኛል። በአጠቃላይ ስለ መምህራኑ
ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል ። ትህትናቸውና ትዕግሥታቸው ከአንዲት እናት ማህፀን የወጡና በአንድ ላይ ያደጉ እስኪመስል ድረስ ይመሳሰላሉ ። የተለያየ ዶክትሪን ያለንን ሰዎች እምነት ሳይነኩ በፍቅርና በትህትና እንደየሁኔታችን ጠቦቱን እንደጠቦትነቱ ፥ ግልገሉን እንደግልገልነቱ ፥ እንዲሁም በጉን እንደበግነቱ በቀስታ እየመሩ እግዚአብሔር ወደሚፈልገው የህይወት ጎዳና መርተውናል / አሳድገውናል ።
ጊዜን መስጠት ከባድ በሆነበት በዚህ የሰሜን አሜሪካ ኑሮ ጊዜያቸውንና ማንነታቸውን ሰጥተው በትጋት እንዳስተማሩን የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ እንደሠሩ ታማኙ አምላክ ደግሞ የእነሱን ቤት እንደሚሠራላቸው አምናለሁ መልካምን ነገር ዘርተዋልና መልካምን ነገር ያጭዳሉ ። በነፃ የተቀበሉትን በነፃ እንደሰጡ እኔም የነሱን ፈለግ እንድከተል ፈጣሪ ይርዳኝ።
በዚህ Bible College የተዋወቅኳቸው ቅዱሳን በጣም በፍቅር የተሞሉ ፤ በዙ የታመቀ የእግዚአብሔር ፀጋ ያላቸው ናቸው። ለወደፊትም አብረን በፀሎት ህብረት ለመቀጠል ወስነናል ። በዚህ የኮሌጁ Alumni ላይ ጌታ በሰጠን ፀጋ በመሳተፍ እናገለግላለን
የዚህ ራዕይ መሥራቾችን እግዚአብሔር አምላክ ይባርክ ።

ከእውቀት አለም የቀዱ ከመንፈስ አለም የተነካኩ ለመሆናቸው እንደኔ ተጠግቶ ወይም እግራቸው ስር ቁጭ ብሎ የተማረ ሰዉ ብቻ ነው እምለውን ሊረዳ የሚችለው
በቪዥን ባይብል ኮሌጅ በመማሬ የተጠቀምኩትን ለመፃፍ በተለይ የእያንዳንዱ አስተማሪ በኔ ላይ ያመጣዉን በጎ ተፅእኖዎች መፅሀፍ ካልፃፍኩኝ በስተቀር በቀላል እሚቋጭ አይደለም።
በአጭሩ ለመናገር ከእውቀት አለም የቀዱ ከመንፈስ አለም የተነካኩ ለመሆናቸው እንደኔ ተጠግቶ ወይም እግራቸው ስር ቁጭ ብሎ የተማረ ሰዉ ብቻ ነው እምለውን ሊረዳ የሚችለው። በተላይ ሁል ጊዜ የሚገርመኝ በጣም የተማሩ እና በጌታ ቤት በማገልገል ብዙ ልምምድ ያላቸው ሆነዉ እንደኔ ያለ ትንሽ የመላምት ሀሳብ ለማንሸራሸር ያላቸው የልብ ስፋት እና ትህትና ልረሳዉ አልችልም።
ይህንን ስል ከልቤ መሆኑን እምታዉቁበትን ቀላል ማስረጃ ላቅርብ። ትምህርት የሚሰጠዉ ከካናዳ ነዉ እኔያለሁት አውስትራሊያ ነው ሰዓታችን ፈፅሞ አይገናኝም ነገር ግን ከለቀቁብኝ መንፈሳዊ ረሃብ የተነሳ ትምህርቴን የጨረስኩት በአዉስትራሊያ ሰአት አቆጣጠር ለሊት ለሊት በአብዛኛዉ 2am-4am ነበር። ያ ማለት ሊነጋ ሲል ነዉ የምተኛዉ።
ሌላው ሳልገልጽ የማላልፈዉ በቪዥን ባይብል ኮሌጅ ተማሪዋች የሚከፍሉት በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ እኔ ደግሞ መማር የጀመርኩበት ጊዜ ወቅቱ በኮቪድ የኢኮኖሚ ጫና ስለነበረ ለኔ ግማሽ ክፍያ ተደርጎልኝ ነዉ የጨረስኩት ለዚህም ጌታ ይባርካቹ ማለት እፈልጋለሁ።
በመጨረሻ ይህንን መልእክቴን የምታነቡ ቅዱሳን በሙሉ እናም እንደኔ ጌታን ለማገልገል እጣ የወደቀባቹ እዚህ ኮሌጅ ገብታችሁ እንድትማሩ በሀይል አበረታታለሁ።
” በኮሌጅ ዉስጥ ሳይሆን ያለፍኩት ኮሌጁ በኔ ዉስጥ አልፎአል “

ህያው የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል መማር ትልቅ መታደል ሲሆን ማንኛውም አማኝ ከጥፋት ወይም ከስህተት ትምሀርት ራሱንም ቅዱሳንን ለመታደግ እንዲማር በጌታ ፍቅር እመክራለሁ።
ብዙ ጊዜ የመፅሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ገብቶ ለመማር ትልቅ መሻት ቢኖረኝም የጌታ ፍቃድ በቪዥይን ባይብል ኮሌጅ እንድማር በመሆኑ ጌታን እጅግ አመሰግናለሁ። “ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ ፊልጵስዩስ 2፡13” - እግዚአብሔር ነውና።
በዚህ አጋጣሚ ብዙ ትምህርትቶችን ተምሬአልሁ የወንጌል ስርጭት ተግባራዊ የሆኑ እርምጃዎች የሆኑትን ለምሳሌ ክርስቶስን የማያውቁ ሰዎች የምትችለውን ያህል ስም ዘርዝረህ ፃፍ፣ በየዕለቱ ፀልይላቸው፣ ለነዚህ ሰዎች ለመመስከር ቀንና ሰዓት ወስን የሚል ጠቃሚና ተግባራዊ እርምጃዎችን በህይወቴ ወንጌል ለሰዎች ለማድረስ ዕውቀትን ጨምሮልኛል።
በተለይም ህያው የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል መማር ትልቅ መታደል ሲሆን ማንኛውም አማኝ ከጥፋት ወይም ከስህተት ትምሀርት ራሱንም ቅዱሳንን ለመታደግ እንዲማር በጌታ ፍቅር እመክራለሁ። በዚህ አጋጣሚ ይህንን ትምህርት ከባለቤቴ ጋር አብረን ስለተማርን ለትዳራችንም ለልጆቻችን የትምህርት አስፈላጊነት እንድናውቅ እረድቶናል። በመጨረሻውም አስተማሪዎቻችንን እጅግ እናመሰግናቸዋለን።

በጣም ተጠቅሜበታለው፣ ተምሬበታለው፣ ተለውጬበታለው፣ ሕይዎቴ ተቀይሯል፣ አድጌበታለው እና እናንተም እንድተማሩ አበረታታለው፡፡ እንዳያመልጣችሁ ተመዘገቡ፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ሰላምታ አቀርባለው
ሥሜ ተማሪ ሪሻን መስፍን ይባላል፡፡ የ ቪዥን ባይብል ኮሌጅ ተማሪ ነኝ፡፡ በዚህ ትምህርት ቤት ለሁለት ዓመት ስማር ብዙ የሕይወት ለውጥ የአይኔ መከፈት አይቼበታለው፡፡ ሕይወቴ ከጌታ ጋር እንዴት መጣበቅ እንዳለብኝ ቤተሰቤ መምራት፣ ልጆቼን በእግዚአብሄር ቃል ለማሳድግ እንዴት እንደምችል በሙሉ ተምሬበታለው፡፡ ጌታን እስከአሁን ድርስ አውቀው ነበር ወይ? እስከምል ድረስ ያስተማሩኝ አስተማሪዎች ሕይወታቸውን ቆርሰው፣ ሕይወታቸውን ራሱ ምስክርነት የሆነ አርአያዎች የሆኑ እንደ እነ ፓስተር ተረፈ፣ ፓስተር አስራት ሌሎችም ብዙዎች ናቸው በጣም ተጠቅሜበታለው፣ ተምሬበታለው፣ ተለውጬበታለው፣ ሕይወቴ ተቀይሯል፣ አድጌበታለው እና እናንተም እንድተማሩ አበረታታለው፡፡ እንዳያመልጣችሁ ተመዘገቡ፡፡
አስተማሪዎቼ ጌታ ይባርካቸሁ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ተባርኩ፡፡

ጌታን እንዴት ሆኜ ማገልገልና ክርስትናን እንዴት ሆኜ እንደምኖር አስተምረውኛል:: ሌሎችም እንድሁ እንደኔ እንዲጠቀሙ እመክራለሁ::
ስሜ ሰሎሞን ተስፋይ ይባላል::
የምኖረው በኣሜሪካ ኮሎምቦስ ከተማ ነው:: የማገለግለው በፊላደልፍያ ወንጌላዊት በቴክርስትያን ሲሆን አገልግሎቴ ቃል በማስተማር እና የቤተክርስቲያኒቱ ሽማግሌ በመሆን ነው:: በቪዥን በግሌ የተጠቀምኩት ነገር ካለ አስተሳሰቤ ሙሉ ለሙሉ መቀየሩ ነው።በጌታ ቤት 27 ዓመት ሆኖኛል። ጌታን ሳገለግለው ብዙ የማውቅ ይመስለኝ ነበር። አሁን ላይ ሆኜ ሳስብና ሳየዉ ግን ጌታ እና ትምህርቱ የማይደረስ መሆኑን ነው የተማርኩት እና በዚህ የነበረኝ ኣስተሳሰብ እንዲቀየር ኮሌጁ ረድቶኛል።
ከአስተማሪዎቼ የተማርኩት ከሁላቸውም ያየሁት ነገር በትምህርቱ የበሰሉና ብቃት ያላቸው መሆኑን ነው:: ከትምህርቱ ይልቅ ግን በፍቅርን እና ትህትና የተመረቁ መሆናቸው ደግሞ አይቻለሁ:: ጌታን እንዴት ሆኜ ማገልገልና ክርስትናን እንዴት ሆኜ እንደምኖር አስተምረውኛል:: ሌሎችም እንድሁ እንደኔ እንዲጠቀሙ እመክራለሁ::

በትምህርቱም የእግዚአብሔርን ቃል በስፋት እንዳውቅና እንዴት መኖር እንዳለብኝ ተምርያለሁ::
ኤልሳ ዘርጋው እባላለሁ:: የምኖረው በኤድመንተን ካናዳ ሲሆን በስራዬ ነርስ ስሆን የማመልከዉና የማገለግለው ደግሞ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ነው:: በዚህ ኮሌጅ በሰርተፍኬትም በዲፕሎማም ተምርያለሁ:: በትምህርቱም የእግዚአብሔርን ቃል በስፋት እንዳውቅና እንዴት መኖር እንዳለብኝ ተምርያለሁ:: ይህም ትምህርት ለመንፈሳዊ ህይወቴ ብቻ ሳይሆን በስራዬም ከሌሎች ጋር ላለኝ ግንኙነት ሁሉ ጠቅሞኛል:: አስተማሪዎችም ያካፈሉን እውቀት ብቻ ሳይሆን የህይወት ልምዳቸውንና ፀጋቸውን በመሆኑ በጣም ተጠቅምያለሁ:: ይህንን እድል ሌሎች እንዲጠቀሙ በብርቱ አበረታታለሁ::

The instructors are not only teachers of God's word, but they are also great examples of the living Christ. I have seen Christ reflected in them, and they taught us from the basis of their own life experiences.
May God's peace and grace be with you all. My name is Adiam Atsbha, and I reside in Maryland, USA. I am a diploma graduate from Vision Bible College (VBC) in Edmonton.
I would like to use this brief statement to describe my incredible and enlightening journey as a student at this college. As its name suggests, VBC is a visionary institution that is making a significant impact on the current generation.
VBC is a place where one gains a deep understanding of God's word and His heart for us as Christians who are good stewards of the Great Commission.
The instructors are more than just teachers of God's word; they are profound examples of the living Christ. I have personally seen Christ reflected in them, and they taught us from the depth of their own life experiences.
Furthermore, VBC features an excellent administration and a well-organized live-stream teaching program. This allows anyone, from literally anywhere in the world, to learn from the comfort of their own home.
The Apostle John wrote, "Jesus did many other things as well. If every one of them were written down, I suppose that even the whole world would not have room for the books that would be written" (John 21:25). Without exaggeration, I feel much like the apostle; I cannot fully share the entirety of my experience and the impact it has had on my life in this brief statement.
If you are genuinely seeking a Bible college, I encourage you to register as soon as possible before it fills up.
GOD BLESS YOU ALL JESUS IS COMING SOON MARANATHA!

ዳዊትም፦ የሥራውን ሁሉ ምሳሌ አውቅ ዘንድ ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር እጅ ተጽፎ መጣልኝ አለ።” 1ኛ ዜና 28፥19
በአለም ላይ በተከሰተው covid19 ምክንያት በብዙ የአገልግሎት ዘርፍ ተጠቂ የነበረችው የክርስቶስ አካል ቤተ ክርስቲያን አንዷ ነች።
በዚህ ትልቅ ተግዳሮቶችን አሳልፋለች ከዚህም በዋነኝነት ደረጃ ህብረት ማድረግ አለመቻል ነበር ።
እኔም እነዚህ ችግሮች ሰከን ባሉበት 2021 አካባቢ ነበር V.B.C በማህበራዊ መገናኛ Facebook ላይ አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ማስታወቂያ ሲነገር የሰማሁት በዚህም ብዙ ርቀት ካሉ ቅዱሳን ጋር ህብረት እንዳደርግ ረድቶኛል።
በነበረኝ የትምህርት ቆይታ በብዙ መልኩ ራሴን በእግዚአብሔር ቃል መመልከት እንድችል የክርስቶስ አካል አገልጋይ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና ለማገልገል ምን አይነት ዋጋ እንደሚጠይቅ እንዲሁም ቤተሰቤን ልጆችን እንዴት አድርጌ መያዝ እንዳለብኝ ረጅም ጊዜ አብሮኝ የኖረውን መፅሃፍ ቅዱስ እንዴት አድርጌ ማጥናት እንደምችል ተምሬበታለሁ ።
ከዛም ባሻገር ካለብኝ የስራ ጫና፣ እንዲህም የትምህርት ሰአት መዛባትና በብዙ ተግዳሮት ውስጥ ሳለሁ ትምህርቱን እንድጨርስ ካደረጉኝ ዋነኛ ምክንያቴ ውስጥ ለእያንዳንዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜ የሚመደቡልን አስተማሪዎች የነበራቸው የማስተማር ብቃት እና ቆይታ- መልካም ወንድሞች፣ ጓደኛ፣ መካሪ፣ እንዲሁም ባለራዕይ መጋቢዎቹ እና ብዙ ፍቅር ያየንባቸው አስተማሪዎች ነበሩ ።
ከእነርሱ በመማሬ ሕይወቴ አንድ ትልቅ ስኬት ላይ እንደደረሰ እቆጥረዋለሁኝ። በዚህ በሰሜን አሜሪካ ያለች የሀገሬ ቤተ ክርስቲያን ብዙ መስራትና ማገልገል እንደ ምትችል፣ ብዙ ሰራተኞች ያሉባት መሆኗን ተረድቻለሁ።
በመጨረሻም ለኤድመንት ቤተክርስትያን መሪዎች ልዩ ምስጋና አቀርባለሁ ።

